Artists

Nigist Fikre (ንግስት ፍቅሬ)

Actress

በርካታ እውቅ ሰዎችን ካፈረችው መርካቶ ሰፈር ነው እድገቷ ንግስት ፍቅሬ። ወደ ትወና የገባችው በወላፍን ተከታታይ ድራማ ነበር በእሱም ዕውቅናን አትርፋለች። ባንዳ'ፍ፣በዛ በክረመት፣ውሃ እና ወርቅ እንዲውም ተውልኝ ፊልሞች ላይ ተውናለች ንግስት ፍቅሬ።

Ayu Girma (አዩ ግርማ)

Actress

ውልደቷም እድገቷ አዲስ አበባ ነው፤ የትወና ፍቅሩ እና ብቃቱ ከክበባት አልፎ ወደ የማለዳ ኮከቦች ውድድር አምጥቶታል። የመጀመርያው የማለዳ ኮከቦች ከተወዳደሩት እስከ መጨረሻው ከተጓዙ አንዷ ናት አዮ፤ ሁለተኛ በመውጣት አጠናቃለች። ከዛም በመቀጠል የማለዳ ኮከቦች ተዋንያን የተወኑበት አጭር ተከታታይ ድራማ እዛው ቲቪ ላይ የተለለፈ ድራማ ፅፋለች፤ በመቀጠል በርካታ አድናቂዎችን ያተረፈችበት ዘመን ድራማ ላይ ሶፍያን ገፀ ባህሪ መተወን ጀመረች። ሼማንደፈር የተሰኘ ፊልም ደሞ ዳይሬክት አድር... read more

Marta Goytom (ማርታ ጎይቶም)

Actress

ውልደት እና እደገቷ አዲስ አበባ ነው፤ ትወናን በሞዴሊንግ ነበር በመቀጠል በዘፍን ክሊቦች ላይ እንደ አክትረስ መሳተፍ ጀመረች ። ከዛም የመጀመርያ ፊልሟን አልሰጥም ላይ ተውነች ። ከዛ በመቀጠል ኤደን፣የህልም ናት፣ስስት ሁለት፣ሰራችልኝ፣የወፍ ቋንቋ፣አስመላሽ፣ፊያሜታ፣ ፍቅር አለ፣ተውልኝ፣እምዬ ጭሶ፣ኪያ ላይ ተውናለች። ወላፍን ቲቪ ድራማ ላይ ነበረች። በ4ተኛው ጉማ አዋርድ በምርጥ ረዳት ተዋናይት በስስት ሁለት አሸንፋለች ማርታ ጎይቶም ።

Kalkidan Tameru (ቃልኪዳን ታምሩ)

Actress

ውልደቷ እና እድገቷ አዲስ አበባ ነው፤ ትወና የልጅነት ህልሟ ነበር ለዚህም በየትምህርት ቤት የሚሰጡ ኮርሶችን ወስደላች ቀጥላም ትያትር ተምራለች ቃልኪዳን ታምሩ። የመጀመርያ ዕይታን በመለከት ተከታታይ ድራማ ኤፍራታ የተባለችን ገፀ ባህሪ ወክላ ታየች፤ በመቀጠልም ሼፋ 2፣ህመሜ፣እምቢ፣ይሁዳ ነኝ፣ፌርማታ፣የልጅ ሀብታም፣አጋዝ፣ጀማሪ ሌባ፣አልሸጥም፣ወደ ልጅነት እና ሀገር ስጪኝ የተወነችባቸው ፊልሞች ናቸው። ለወደዱት የተሰኛ ተከታታይ ቲቪ ድራማ ላይ አሁንም እየተወነች ነው።

Nuhamin Meseret (ኑሃሚን መሰረት)

Actress

ኑሃሚን መሰረት በ አዲስ አበባ ዮሴፍ አከባቢ ተወለደች። ምንም እንኳን “በህግ አምላክ” ለመጀመርያ ጊዜ በትወና የተሳተፈችበት ቢሆንም የትወና ተሰጦ እንዳላት አሳይታበታለች።

Biniam Sebho (ቢንያም ሰብሆ)

Binyam Sebho a young talented artist graduated from Addis Ababa university college of performing and visual arts. known for his acting at "Meleket" series drama and his directing of different music videos, commercials, TV shows and documentaries. his master-pies for directing is the kana original series documentary... read more

Solomon Muhe (ሰለሞን ሙሄ)

Actor | Director | Writer

ደራሲ፣ዳይሬክተር፣ተዋናይ እና ፕሮዲሰር ሰለሞን ሙሄ ውልደቱም እድገቱም አዲስ አበባ ነው። በጣም በወጣትነቱ ነው ወደ ትወና አልያም ወደ ጥበብ የገበው፤ እንደ እኔ አገለላለፅ ሰለሙን በተለይ በፊልማችን ላይ በጥሩ ሆነ በመጥፎ ብቻ አሁን ላለበት ደረጃ የራሱን ነገር ያበረከተ ባለሙያ ነው።
በ1994 ማግስት የተባለ ፊልም በድርሰት፣ በዝግጅት፣ ትወና፣ ፕሮዲሰር አልፎም ተርፎ ማጀብያ ሙዚቃ በመስራት ለህዝብ አቅርቦል ከዛም በፊት በአጃቢነት ትንሽ የማይባሉ ስራዎችን ሰርቷል።
መ... read more

Pina Abay (ፒና አባይ)

Actress

Pina was born in Ardaita, a place near Adama (Nazreth), and she moved to Adama. As a kid, her dream to be an actress made her to watch a lot of movies. She started her acting career in music video clip in Adama, and her first movie was Valentine. In addition to her acting career, Pina also has B.Sc in Computer Engi... read more

Sonia Noel (ሶኒያ ኖዬል)

ሶኒያ ኖዬል አድናቂዎቿ የሚያውቋት ቪዳ በሚለው የመጀመሪያ የፊልም ካራክተሯ ነው። ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበባ ጎፉ ካንፕ ነው። በ በ lion tourism and hotel management በ tour guide ለብዙ አመታት ሰርታለች። ከዛ በኋላ ነው ወደ ፊልም ኢንዱስትሪ ላጋጣሚ የገባችው ከዚ በፊት በዚ ሙያ ተምራም ሰርታም ባታውቅም የመጀመሪያ ስራዋን "ቪዳ" ፊልም በ writing , producer and acting ነው የጀመረችው። ቀጥሎ የሰራዋቸው ፊልሞች ቪዳ እስክትመጪ ልበድ ... read more

Leulseged Kassa (ልዑልሰገድ ካሳ)

በትወና ዲፕሎማና cocያለው የተቀበረው ተከታታይ ድራማ ላይ በትወና ብሌን አቻዬ እኔና ቤቴ ፊልም ላይ በትወና የተሳተፈ ሲሆን በፕሮዳክሽን ማናጀርነትም ይሰራል

Tseganesh Hailu (ፀጋነሽ ሀይሉ)

Actress | Producer

ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበባ ነው ወደ ትወና ከመግባቷ በፊት ሞዴል ነበረች፤ ከሞደሊንግ ወደ ትወና ከመጡ በርካታ እንስት ተዋንያን ውስጥ ናት። ስጦታ፣ውበት ለፈተና፣ሶስት ማዕዘን፣ረብኒ፤ የመሀን ምጥ፣ሰላም ነው?፣የእግዜር ድልድይ እና የአርበኛው ልጅ 2 የተወነችባቸው ፊልሞች ናቸው። ሰላም ነው? እና የአርበኛው ልጅ ሁለት? ፊልሞች ደሞ ፕሮዲሰር ናት። በ7ተኛው አዲስ ሙዮዚክ አዋርድ ላይ በምርጥ ተዋናይት በሰላም ነው? ፊልም አሸናፊ ናት ፀጋነሽ ሀይሉ።

Daniel Tegegn (ዳንኤል ተገኝ)

Actor | Writer

ተወልዶ ያደረገው አዲስ አበባ ነው ወደ ትወና ሙያ የገባው በፍላጎትም በአጋጣሚ ጭምር ነው፤ ተስፋዬ አበበ (ፋዘር ቤት) ጋር ወደ ትወና አለም ለመግባት ድልድይ ሆኖታል የመጀመርያ ስራውን ህይወት ፊልም እዛው ቤት እያለ ሰራ ከዛም የአውሬ እርግቦች፣የተፈነ ፍቅር፣ትስስር፣እህት፣ተስፈኞቹ፣ሰውዬው፣ማክቤል፣የሴም ወርቅ፣እንደ ሀበሻ፣ሄዋን ስታፈቅር እና ወደኃላ ላይ ተውኖል። የሴም ወርቅ ፊልም ላይ ከትወና በተጨማሪ ደራሲ እና ፕሮዲሰርም ገመና ሁለት፣ሞጋቾች እና የማዕበል ዋናተኞች ደሞ እሱ በትወና የተሳ... read more