Blogs & Articles

79. The Movie! (መሥራት ጀግንነት ነው፤ ማድነቅ መሰልጠን ነው!)

ይህ ተካበ ታዲዎስ ፤ (ይህ የጥበብ ገበሬ) ‹79 - ሠባ ዘጠኝ› ፊልም ይዞ እየመጣ ነው ተካበ ታዲዎስ ይባላል፡፡ ልጅ እያለ ለሚያያቸው ፊልሞች ከፍተኛ ፍቅር ነበረው፡፡ ለእናቱ ፈለቀች ጌታሁን የልጅነት ሕልሙን ይነግራት ነበር፡፡ ‹‹እቴቴ … ትልቅ ስሆን ፊልም ሰሪ እሆናለሁ›› ይላታል፡፡ እናቱም ‹‹እንዳፍ ይሁንልህ ልጄ!›› ብሏው መርቀዋለች፡፡ የእናቱ ምርቃት እዚህ ደርሷል … የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን እንዳለፈ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመደበና የኢኮኖሚክስ ትምህርቱን መከታተል ጀመረ፡፡ በ1999 እና በ2000 ዓ.ም. በዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለ በትርፍ ጊዜው ፊልም ኤዲቲንግ እና ካሜራ ቀረጻ እየተለማመደ ሁለት የተማሪ ፊልሞችን ሰራ፡፡

ትምህርቱን እንደጨረሰ በትምህርት ሚኒስቴር በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ሆኖ ተቀጠረ፡፡ ነገር ግ...

Ethiopian actress Fryat Yemane won Best Independent Actress on HAPA (ፍርያት በHapa አሸነፈች)

ባለፈው ፍርያት በHAPA እጩ መሆንዋን ገልጸን እንደነበር ይታወሳል። በትናንትናው እለት ፍርያት በInstagram ፔጇ ላይ ሽልማቷን ይዛ ባማረ አለባበስ ፎቶዋን ለደጋፊዎቿ ሼር አርጋለች። Team EtMDB እንኳን ደስ አለሽ ደስ ብሎናል ለማለት ይወዳል።
The beautiful actress received HAPA film award in California.

The Weeknd Cuts Ties with H&M (አቤል ተስፋዬ ከH&M ጋር የነበረውን ኮንትራት ኣቋረጠ)

ታዋቂው የስዊድን የልብስ አምራች ኩባንያ H&M ብዙዎችን ያስቆጣ የሁዲ ሹራብ አንድ ጥቁር ህጻን ተለብሶ በላዩ ላይ "Coolest monkey in the jungle" የጫካው አራዳ ዝንጀሮ የሚል ጽሁፍ ይነበብበታል። ይህ ምስል ብዙዎችን አስቆጥቷል። እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2016 ጀምሮ ወኪል የነበረው ኢትዮጵያ ካናዳዊው አቤል ተስፋዬ(The Weeknd) በሁነታው እንዳልተደሰተና ከH&M ጋር የነበረውን ኮንትራት እንደሚያቋርጥ በሶሻል ሚድያ ላይ አስታውቋል። H&M ወድያዉኑ የሁዲውን ሽያጭ ከUS ገበያ አንስተውታል። ኩባንያው ለፒትፎርክ በተሰጠው መግለጫ ላይ "ይቅርታ, ብዙ ሰዎች ስለ ምስሉ በጣም የተበሳጩ መሆናቸውን እገነዘባለን.እኛ በ H & M መሥሪያ ቤት ውስጥ የምንሠራው እኛ ተስማምተን እንሰራለን. ስለዚህ ትክክለኛውን ህትመት መመለስን እናሳያለን, ስለዚህ ምስሉን ከ...